Mizan-Tepi University
       Light of the green valley!

Tepi Fresh Students Welcome
 
» Page 4
Sort articles by: date | rating | read | title

ዶ/ር አሚር አማን የኤፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚንስትር የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታልን ጎበኙ፡፡

Author: Admin dated 20-09-2019, 14:41
 • Dislike
 • 0
 • Like
ዶ/ር አሚር አማን የኤፌዴሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚንስትር የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታልን ጎበኙ፡፡


እንደ ሀገር መንግስት ትኩረት ሰጥቶ የማህበረሰቡን የአገልግሎት ተጠቃሚነት ከፍ ለማድረግ እየሰራባቸው ከሚገኙት 22 ሆስፒታሎች አንዱ የሆነውን የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የማስፋፊያ ግንባታ ስራዎች ማለትም የጨቅላ ህጻናት እና የእናቶች ማቆያ ማዕከል እንዲሁም አጠቃላይ የሆስፒታሉን የስራ እንቅስቃሴ በባለሞያዎች የተደረገላቸውን ገለጸ አዳምጠዋል፡፡


ክቡር ሚኒስትሩ በያዝነው አመት ስራው ተጠናቆ የሚዛን -ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎችን በማስተማሪያ ሆስፒታሉ ለማካተት በማለት እየተገነቡ የሚገኙትን የተማሪዎች ማደሪያ፣ ቤተ-መጽሀፍ፣ መማሪያ ክፍሎች እንዲሁም የመሰረተ-ልማት ዝርጋታ ስራዎችንም ጎብኝተዋል፡፡
ከመስክ ጉብኝት በኋላ በነበረው አጭር የውይይት ጊዜም አቶ አስራት አሰፋ የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳዳሪና የዩኒቨርሲቲው አስተዳዳር ቦርድ አባል በጤናው ዘርፍ በዞኑ ከሚስተዋኑ አበይት ተግዳሮቶች አበይት የሆኑትን በዝርዝር ለክቡር ሚኒስትሩ አቅርበዋል፡፤ በየደረጃውም የሚገኙ የዘርፉ ሀላፊዎች እና የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል በበኩላቸው ጉብኝቱን ክቡር ሚኒስትሩ ትኩረት ሰጥተው ማድረጋቸውን አድንቀው ማንሳት በሚገባቸው አበይት ነጥቦች ላይ ሀሳቦቻቸውን ሰንዝረዋል፡፡

Author: Admin dated 3-07-2019, 10:00
 • Dislike
 • -1
 • Like
የግዢና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በንብረት አያያዝና አመዘጋገብ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ


በቴፒ ግቢ ለሚገኙ የንብረት ክፍል ሰራተኞች አዲሱ የስራ ምደባ JEG ጋር ተያይዞ ወደ ንብረት ክፍል አዲስ ተመድበዉ ለመጡ ሰራተኞች ስለ አላቂ ንብረት አመዘጋገብ፣ የቋሚ ንብረት መለያ ቁጥር አሰጣጥ፣ ስለ ሞዴል አቆራረጥ፣የእስቶክ ካርድና የቢን ካርድ አጠቃቀም በመሳሰሉት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የICT ልማት ጽ/ቤት ማስተባበሪያ ለቤተ-ሙከራ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ

Author: Admin dated 3-07-2019, 09:53
 • Dislike
 • 0
 • Like
የICT ልማት ጽ/ቤት ማስተባበሪያ ለቤተ-ሙከራ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ
በቤተ-ሙከራ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ማሽኖች የሚታይባቸውን ትናንሽ ችግሮች ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞቹ ስራቸውን እየሰሩ እዚያው ማስተካከል እንዲችሉ በቢሮ ማሽን የላፕቶፕ፣የኮፒ ማሽንና የፕሪንተር ጥገና፣በኔትዎርኪንግና በቀለም መሙላት በመሳሰሉት ነጥቦች ላይ በገለጻና በተግባራዊ ልምምድ በማስደገፍ ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡

Author: Admin dated 3-07-2019, 09:43
 • Dislike
 • +1
 • Like
ሀገር አቀፍ የፅዳት ዘመቻ በቴፒ ግቢ ተከናወነ
የኢ.ፌ.ድ.ሪ ጠቅላይ ሚንስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያወጁትን የፅዳት ዘመቻ ምክንያት በማድረግ ንፁህ ግቢና አከባቢ ለንፁህ ማህበረሰብና ጥራት ላለው ትምህርት በሚል መሪ ሀሳብ የሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የቴፒ ግቢ ማህበረሰብ በቀን 6/8/2011ዓ.ም በግቢ ውስጥ በመሰባሰብና በተለያየ አቅጣጫ በመሰማራት የግቢውን ውበት የሚያበላሹ የወዳደቁ ብረታብረቶች፣የተዘነጠሉ የዛፍ ቅርንጫፎችንና ስብርባሪ እንጨቶችን በማንሳትና ቦታ ቦታቸውን እንዲይዙ በማድረግ እንዲሁም ያልፀዱ ቦይዎችን በማፅዳት ግቢው ውብና ማራኪ እንዲሆን ተሳትፎ በማድረግ አሻራቸውን ጥለዋል፡፡
የፅዳት ዘመቻው ተሳታፊዎችም በበኩላቸው አዋጁን ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ተሳትፎ በጣም መደሰታቸውን እየገለፁ የፅዳት ዘመቻው በአዋጅ ብቻ ሳይሆን በግቢያችን ውስጥ ፕሮግራም በማዘጋጀት በየወሩ ዘመቻ በመውጣት ከፅዳት ሰራተኞች በተጨማሪ እገዛ በማድረግ ግቢያችንን ውብና ማራኪ እንዲሆን ቀጣይነት ያለው ዘመቻ መሆን አለበት ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የምህንድስናና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ሰባተኛውን የትምህርት ክፍል ለመክፈት በዝግጅት ላይ መሆኑን አሳወቀ

Author: Admin dated 3-07-2019, 09:39
 • Dislike
 • 0
 • Like
በምህንድስናና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ስር ኢንዱስትሪያል ምህንድስና ትምህርት ክፍል ለመክፈት የመካኒካል ምህንድስና ትምህርት ክፍል ሀላፊ መ/ር ማስረሻ አዳሾ እና የመካኒካል ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህር፣የዩኒቨርስቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ዳይሬክተር እንዲሁም አዲስ ለሚከፈተው ትምህርት ክፍል ካሪኩለም አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት መ/ር ተረፈ ጅማ በጋራ በመሆን አዲስ ስለሚከፈተው ትምህርት ክፍል የዳሰሳ ጥናት በማዘጋጀት ሙሉ የትምህርት ክፍሉ መምህራን በተገኙበት ሰነዱን ለዉይይት አቅርበዋል፡፡

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ በተማሪዎች መረጃ መቆጣጠሪያ ዘዴ/SImS/ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

Author: Admin dated 3-07-2019, 09:32
 • Dislike
 • 0
 • Like
ዩኒቨርስቲው የተማሪዎች መረጃ በተጠናከረ መልኩ ዘመናዊ በሆነ ዘዴ ተግባር ላይ እንዲውል ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ አዲስ ሶፍት ዌር የገዛ በመሆኑ አጠቃቀሙን ለትምህርት ክፍል ሀላፊዎችና ለመምህራኖች በሬጅስትራል ጽ/ቤት አዘጋጅነት ከ19-21/7/2011 ለሶስት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

Up