ዩኒቨርስቲው የተማሪዎች መረጃ በተጠናከረ መልኩ ዘመናዊ በሆነ ዘዴ ተግባር ላይ እንዲውል ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ አዲስ ሶፍት ዌር የገዛ በመሆኑ አጠቃቀሙን ለትምህርት ክፍል ሀላፊዎችና ለመምህራኖች በሬጅስትራል ጽ/ቤት አዘጋጅነት ከ19-21/7/2011 ለሶስት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የስልጠናው ተሳታፊዎች
የስልጠናውም አላማ በተማሪዎች ውጤት አያያዝና በፈተና አዘገጃጀት ከወረቀት ስራ ተላቆ ወደ ቴክኖሎጂ በማስገባት አሰራሩን በማዘመን የጊዜን፣የጉልበትንና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ብክነት የሚቆጥብ ነው፡፡
በስልጠናውም ሂደት አንድ የትምህርት ክፍል ሀላፊና አንድ መምህር ምን መስራት እንዳለባቸው፣እንዴት መስራት እንዳለባቸውና ምን እንደሚጠበቅባቸው በሶፍት ዌሩ ውስጥ የተካተቱ በመሆናቸው ስለአጠቃቀሙ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል፡፡

አሰልጣኞች
የስልጠናው ተሳታፊዎችም የሶፍት ዌሩ ስልጠና ጊዜንና ጉልበትን የሚቆጥብ ስህተትን የሚያርም ባለንበት ቦታ ሁነን ስራችንን እንድንሰራ የሚረዳን ጠቃሚ ስልጠና ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡አክለውም ስልጠነናው በኢንተርኔት የሚሰራ ሶፍት ዌር በመሆኑ የኢንተርኔትና የመብራት መቆራረጥ ያጋጠማቸው ተግዳሮት እንደነበረም ገልፀዋል፡፡
የስልጠናው አዘጋጅ እንደገለፁት ሶፍት ዌሩ የሬጅስተራር ስራዎችን የሚያቀላጥፍ በመሆኑ የ2010 እና የ2011ዓ.ም የተማሪዎች ውጤት ኦን ላይን ገብቶ ተግባር ላይ የዋለ እንደሆነና ከ 2009ዓ.ም በኋላ ያለውን የተማሪ መረጃ በቀጣይ ኦን ላይን ላይ እንደሚያሰገቡና ከአመራር ጀምሮ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ቀጣይነት ያለው ስልጠና እንደሚያዘጋጁ ጠቁመዋል፡፡

የስልጠናው አዘጋጅ አቶ ሀሊድ አብዱ