በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የጥናትና ምርምር እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክት ትልመ ጥናት (proposal) በኮሌጁ ተመራማሪ መምህራን በመቅረብ ላይ ነው ፡፡
ጥር 14/2012 ዓ/ም

በአካባቢው ከሚገኙ አጎራባች ዞኖች የተውጣቱ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በሚገኙበት ዛሬ በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ በተዘጋጀው ፕሮግራም 40 የጥናትና ምርምር እንዲሁም 15 የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክት ትልመ ጥናቶች ይፋ የሚደረጉ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ማህበረሰበረ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ገልጽዋል ፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ከዩኒቨርሲቲው ውጭ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት እና የምርምር ተቋማት መገኘታቸው የጥናትና ምርምር ድግግሞሽን ከማስቀረቱ ባሻገር ከነዚህ አካላት ጠቃሚ ግብዓት ለማግኘት አጋዥ እንደሆነ ጽፈት ቤቱ አክሎ ገልጽዋል፡፡