የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ የተማሪዎች ህብረት 3 የተማሪዎች ምግብ ቤት ኮሚቴ አባላትን አስመረጠ፡፡
ህዳር 9 /2012 ዓ/ም
ከ400 በላይ ተማሪዎች በኮሚቴ አባልነት ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት በታየበት የምርጫ ውድድር የተለያዩ የማወዳደሪያ መስፈርቶችን ያለፉ 6 ተማሪዎች ቢመረጡ የሚመሩበትን የወደፊት እቅድ በተሰጣቸው የ5 ደቂቃ ጊዜ አቅርበዋል፡፡
በዚህም መሰረት ተወዳዳሪው በዩኒቨርሲቲው የምግብ ቤት ያለውን የምግብ አገልግሎት አሰጣጥ አሁን ካላው የበለጠ ለማሻሻልና ችግሮች ቢፈጠሩ ችግሩን ከሚመለከተው የዩኒቨርሲቲ አካል ጋር ለመፍታት ያዘጋጀውን ስልት፣ ችግሮችን በውይይት የመፍታት እና ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲን በሰላም አንባሳደርነቱ ለማስቀጠል ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም ሌሎች ተግባሩን ባቀረበው እቅድ መሰረት መራጩ ተማሪ ከተመለከተ በኋላ በመጨረሻ በተሰጠው ድምጽ ብልጫ ያገኙ እና አሸናፊ የሆኑ 3 ተማሪዎች ታውቀዋል፡፡