ለሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ነባር እና አዳዲስ ተማሪዎች በሙሉ ከዚህ ቀደም የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች የመግቢያ ቀን መስከረም 21 እና 22 የነበረ ቢሆንም በት/ት ሚኒስቴር በተዘጋጀው አዲሱ የት/ት የፍኖተ-ካርታ ዙሪያ በሚደረገው ውይይት ጋር የፕሮገራም መደራረብ በመከሰቱ ላልተወሱ ቀናት መራዘሙን በቴሌቪዥን ጭምር ያሳወቅን ቢሆንም በአንዳንድ ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች የ2011 የተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 2 እና 3 /2011 መሆኑን እየገለፁ ሲሆን መረጃው ሀሰተኛ እና ትክክለኛ የዩኒቨርሲቲው መረጃ አለመሆኑን እያሳወቀን የዪኒቨርሲቲያችን የሁለቱም (የዋናው እና ቴፒ) ካምፓሶች ተማሪዎች ትክክለኛው ቀኑን በEBC ፣ የዩኒቨርሲቲው ዌብ ሳይት (www.mtu.edu.et) እንዲሁም በፌስቡክ አካውንት ይፍ እስከሚደረግ በሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ ሀሰተኛ መረጃ ከዩኒቨርሲቲው የመቀበያ ወቅት ቀድማችሁ ጉዞ እንዳትጀምሩ እና ላልተፈለገ ወጪ እንዳትዳረጉ ለማሳሰብ እንወዳለን