የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል ከፌደራል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የድጋፍ እና ክትትል ዳይሬክቶሬት በተውጣጡ 5 ከፍተኛ ባለሙያዎች ከመጋቢት 24-25/2010 ዓ.ም የተጎበኘ ሲሆን የማስተማሪያ ሆስፒታሉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተክለማርያም እርገት የድጋፍ እና ክትትል ቡድኑንን በመቀበል በቢሮቸው ከማናገርም ባለፈ የማስተማሪያ ሆስፒታሉ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱ በፌደራል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ ሙሆኑን አለመሆኑን በትክክል በድጋፍ እና ክትትል ቡድኑ እንዲገመገም ያደረጉ ሲሆን ፤ ለድጋፍ እና ክትትል የመጡት ከፍተኛ ባለሙያዎችም በአራት ምድብ በተከፈለው እና ሁለት ቀናትን በፈጀው ጉብገኝታአው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሆስፒታሉ ያሳየውን በርካታ መሻሻልሎች ያደነቁ ሲሆን በህክምናው ቋንቋ የ ‘ CRC Ambassador ‘ በየዘርፍ ከመቀመጣቸውም በላይ የማበረታቻ ሽልማት መኖሩ ፣ ከሲኔር ስታፍ የተውጣጣ አድቫይዘሪ ቦርድ መኖሩ ፣ የቲቺንግ ሆሰፒታልሉ የክሊኒካል ኤርያ ከሌሎች የሀገራችን የህክምና ቋማት በበተለየ ፅዱ እና ሽታ አላባ በመሆኑ እና አብዛኞቹ የአገልግሎት አሰጣጦች ስታንዳርድ የተዘጋጀላቸው መሆኑን አድንቀው ሊሻሻል ይገባል ያሉትን የህክምና ክፍሎች ጥበት ፣ ያልተሟሉ የላብራቶሪ ኬሚካሎች ጉዳይ አንስተዋል፡፡